ደዌያችንን ፈወሰልን ሀሌሉያ
በፀጋና በምህረቱ ሀሌሉያ
ከዘላለም ሞት ተቤዠን ሀሌሉያ
ለክብሩ እንድንኖር ሀሌሉያ
የምስጋናን መስዋዕት ወደቤትህ ደስ እያለን እናቀርባለን
ለስምህም ክብር ሁልጊዜ በደስታ እንዘምራለን
ሀሌሉያ/2/
ኑና እግዚአብሔርን እናመስግን
ሀሌሉያ/3/
ላመስግነው/2/ ለኔ የሞተውን በግ
ክብር ስጡ ሰዎች ሁሉ
በደሙ አንጽቶናልና
አልተረሳሁም/3/ በስሜ ያውቀኛል/2/
ኦ ያውቀኛል
ሁሉ በሁሉ ነን ምንም አይጎድለንም
በሰማይ ቤት ስቃይ ጉስቁልና የለም
እንዘምራለን ዘላለም በደስታ
ለይሁዳ አንበሳ ሞትን ድል ለነሳ
ናፍቃለሁ ያንን ቀን ላይ ሁልጊዜ ሮጣለሁ
የተሰቀለውን የሞተውን የተነሳውን ላየው
የመላእክት ድምፅ ዝማሬአቸው ከሩቅ ይሰማኛል
ምጠብቀው ጌታ የሱስ መምጫው ጊዜው ደርγል
ሃያላን ሲነሱ እርስ በእርሳቸው
ምድር ስትናወጥ ግራ ሲገባቸው
ቀኑ ሲደርስ ግን አንተ ስትመጣ
ያን ጊዜ ያበቃል የዚች አለም ጣጣ
ጌታ ሲመጣ በመላእክት ታጅበን
ከሙሽራው ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለን
የሚያሰጋን የለም እዳችን ሁሉ ተከፍሏል
በነፃነት ልንኖር ከርሱ ጋር ዳግመኛ በክብር ይመጣል
ሸክሜን እና ጭንቀቴን
በፊትህ ይዤ ቀርባለሁኝ
ያለፈው ይበቃኛል
መለወጥን እሻለሁ
ጌታ ሆይ
የልመናዬን ቃል ስማ ጸሎቴንም መልስልኝ
እጅህን ዘርግተህ ታደገኝ
በራሴ ብዙ ደክሜአለሁ ስለፋ
የማላውቀውን በተስፋ
እድሜዬን ሁሉ ስገፋ
ያንተን የልብህን ሀሳብ እየፈጸምኩኝ መኖር እሻለሁ
ከዚች አለም ከንቱ ነገር ላይ አይኔንም አነሳዋለሁ
ዋጋ አለውና የከበረ እሱን ለመያዝ እዘረጋለሁ
እንግዲህ በቀረኝ እድሜ ክብርህን ማየት እሻለሁ
ባለማስተዋል የሰበሰብኩት
ከንቱ ብቻ ነው ለካስ ያከማቸሁት
ጥፋቴን ሁሉ ዞር ብዬ ሳየው
እራሴን ስወቅስ ደግሞ እገኛለሁ
ደግሞ እንደገና ነግቶልኝ ስሮጥ
አንድ አይነት ህይወት የማይለወጥ
ይህ ከንቱ ኑሮ ብዙ ደከመኝ
አሁን ግን በቃኝ እባክህ ለውጠኝ
በማዕበል ውስጥ ሆኖ ካንተ ጋራ መሔድ ነው/2/
በወጀቡ መሀል ካንተ ጋራ መሔድ ነው/2/
በባህር ላይ ሆኖ ካንተ ጋራ በሚያስፈራራው
ተሸመድምዶ መቅረት ለምንድነው ግራ ሚያጋባው
ከቶ ለምን ይሆን ካንተ ጋራ የምንፈራው
የዘወትር ልመና አሀሀሀ የምናለቅሰው
ጌታ ሆይ እባክህ አይኖቻችንን ክፈተው
በእውነት ከኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው
አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጎናችን
እንፈራለን ወጀቡን እያየን
እምነታችንን በሁኔታዎች ጥለን
ወየው ጠፋን እያልን እንጮሀለን
ከእንግዲህ ካንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን
ወጀቡን አንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን
ለአእዋፍ ሁሉ አሀሀሀ የምታጠግብ ነህ
ለኛ ለልጆችህ ደግሞ እንዴት ትነሳለህ
ብታደርግ ሁልጊዜ አሀሀሀ መች እናውቅሀለን
ስለሚቀጥለው ደግሞ ብዙ ሀሳብ አለን
ጌታ አንተን ብናይህ አሀሀሀ ይህ ባልሆነ በኛ
እምነት ጨምርልን ጌታ ሆይ አናውቅህምና
ሃጢአተኛ ነበርኩ አለም ጉድ ያለልኝ
ለሰራሁት በደል ሞት የፈረዱብኝ
ገመናዬን ገልጠው እየገፈተሩኝ
ለፍርድ አቀረቡኝ በድንጋይ ሊወግሩኝ
ዳኛው ግን ስለኔ በእውነት አዘነልኝ
ውስጡን እያወቀ ለኔ ፈረደልኝ
ከከሳሾቼ እጅ በጥበብ አስጥሎኝ
በኔ ፋንታ እሱ ሞቶ ከፈለልኝ
በምህረቱ ዛሬ ቆሜአለሁ
ስለኔ ሞቶ እኔ ድኛለሁ
ነፍሴን ከሚሹ ከጠላቶቼ
ማምለጥ ችያለሁ ምህረት አግኝቼ
የምህረቱ ብዛት ከባህር ይጠልቃል
ስለሃጢአተኛው በእውነት ግድ ይለዋል
እሱ ነው ዳኛዬ የሆነኝ ጠበቃ
ቀድሞ የታደገኝ ህይወቴ ሲያበቃ
ከሳሾቼ ሁሉ ድንጋያቸውን ጥለው
ወደኋላ ሸሹ ህሊና ወቅγቸው
እዳዬን ከፍሎታል አሁን ነፃ ሰው ነኝ
ላዳነኝ ኢየሱስ እዘምራለሁኝ
ዋጋዬ ይህ ነው በእሱ ደም ታጥቤአለሁ እኔ ድኛለሁ
ስለኔ ሞቶ አድኖኛል በሱ ቁስል ተፈውሻለሁ
ነፍሴን ከሚሹ ከአዳኝ ወጥመድ አስመለጠኝ እኔን አዳነኝ
ዛሬ በደስታ ዘምራለሁ በርሱ ቁስል እኔ ድኛለሁ
ፍቅሩን እያሰብኩ በፊቱ ዘምራለሁ
ለነፍሴ መዳን ሆኖላታልና ስሙን እባርካለሁ
ምህረቱን እያሰብኩ በፊቱ ዘምራለሁ
ከሞት አፍ ከጫፍ ላይ አውጥቶኛልና ታሪኬን አወራለሁ
ድግስ አዘጋጅል ንጉሱ በይፋ
ያላወቀ ሁሉ በከንቱ እንዳይለፋ
ለሚገባ ሁሉ በእውነተኛው በር
መንገዱ አንድ ነው የለም ከርሱ በቀር
ልብሳችንን አጥበን አንጽተን በደሙ
ተግተን እንጠብቀው ቅርብ ነው ሰዓቱ
አንድ ቀን አምላኬን እገናኘዋለሁ
ሚያየኝን ጌታ ባይኔ አየዋለሁ
ከደመና ከፍ ካለው በላይ ሄዳለሁ
ዘላለም ከርሱ ጋር እኖራለሁ
እንዴት ብሩህ ቀን ነው ጌታን የማይበት
ከዚህች አለም ስቃይ ከቶ የማርፍበት
ኢየሱስ ይመጣል ታጅቦ በክብር
አብረን እንሄዳለን ልንኖር ከርሱ ጋር
ሰምቼ ነበረ ስታንኳኳ በሬን
ግን አላስተዋልኩም አንተ መሆንህን
ብዙ አድክሜሀለሁ አውቃለሁ እራሴን
ግን እራርተህልኝ ቤቴ ትመጣ ይሆን
ጠብቅሀለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ
በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመጣ
ድምጽህን አሰማኝ ልቤ እንዲጽናና
ግን አንተ ዝም ካልከኝ እፈራለሁና
ዝም ስትል ጊዜ ስታጠፋ ድምጽህን
ያሰብኩት በሙሉ እንዳልነበር ሲሆን
ቀኑ ሲጨላልም ፈርቼ ሁኔታን
መልእክት ልኬ ነበር ትመጣ ይሆን የሚል
እንግዳዬ የሱስ እረፍ ቤቴ ገብተህ
ብዙ ምነግርህ አለኝ ማጫውትህ
ልቤ ያንተ ቤት ነው ሀሳብህን ፈጽም
እጠብቅሀለሁ ከቶ አልሰለችም
ጓዴ የሱስ እስቲ ና
የማዋይህ አለኝና
ድሮ ገና በማህጸን ሳለሁ በእናቴ ሆድ
በስም ጠርተህ የለየኸኝ ክፉ ደጉን ሳላውቅ
የአንተ ክብር መገለጫ እንድሆን በቤትህ
ከነሀጢአቴ የመረጥከኝ ላንተ እንድኖርልህ
ስመላለስ በዚህች ምድር ሳገለግል አንተን
የማልኖረውን አውርቼ የተጣልኩ እንዳልሆን
እንዳታልፈኝ እፈራለሁ በምትመጣበት ቀን
ህይወቴም አንተን ያክብርህ አፌ ብቻ ሳይሆን
ሀይልህ ይርዳኝ ለምናለሁ
እንድትረዳኝም አምናለሁ
መልካም ነገር ያደረኩ መስሎኝ
ሳሳዝንህ እንዳልገኝ
በሰጠኸኝ መንገድ ስሔድ ባሰብክልኝ ስፍራ
እንዳልገኝ ሳሳዝንህ ቸል ብዬ ሳልሰራ
ዛሬ በቀን ለምንሀለሁ ሀይልህ እንዲረዳኝ
በመክሊቴ ብዙ አትርፌ አንተን ደስ እንዳሰኝ
ክብርህን አሳየኝ የአንተን ማንነት
ቅዱሱን መንፈስህን ሚመራኝ ወደ እውነት
እኔ ደካማና ሀጢአተኛ ሰው ነኝ
ሀይልህ ግን ከረዳኝ በእግሬ ቆማለሁኝ
ቀድመህ ውጣ በህይወቴ
ልከተልህ ቸሩ አባቴ
አንተ ቀድመኸኝ ካልወጣህ
እኔ ብሮጥ ምን ላመጣ
ማረፍያ ቤት የላቸው ጌጣ ጌጥም ቢሆን
ፍቅር ግን አላቸው ለሚጠባበቁት ህፃን
ባንድ ምሽት ተወለደ በሁለት ከተሞች መሀል
በከብቶች በረት አገኙት ሰማይ ዝቅ ያለ ይመስላል
አዲስ ኮከብ ያበራል በላይ ከፍ ካለው ሰማይ
በብርሀን በዚያ ክረምት ፍቅር ሰላምን አገኙ
ይህን ፀጋ ብንሻ ህይወት ይሆነናል
አሁንም ይህ ብሩህ ኮከብ ያበራል
ስፍራ አጣ ይህ ጌታ በፈጠራት አለም ውስጥ
ራሱን ዝቅ አድርጎ መጣ የአለማት ንጉስ
ብርዱ ጨለማው ረሀቡ ሊወስድ አልቻለም ደስታቸውን
መውጫን ያዘጋጃል ጌታ ለውዱ ህፃኑ
ኦ ቅዱስ ሌት ከዋክብት ያበራሉ
ያዳኛችን ልደት ስለሆነ
አለም በሃጢያት ውስጥ ስትጨማለቅ
መጣላት ተስፋዋን ስትጠብቅ
ግሩም ተስፋው ነፍሳችንን ያረካል
ደስ ይበለን ንጋት ሆኖልናል
ስገዱለት የመልአኩን ድምጽ ስሙ
በቅዱስ ሌት በክርስቶስ ልደት
ቅዱስ መዝሙር ለርሱ አቅርቡለት
በእምነት ኃይል በብርሀኑ ተመርተን
በደስታ ልብ እንይ ያንን ህፃን
የኮከቡን ብርሀን አይተው ሲሮጡ
ጥበበኞች ከሩቅ ሀገር መጡ
ህፃኑ ንጉስ በበረት ተኝል
በችግርም ወንድማችን ሆኗል
የኛን ሀሳብ ድካማችንን ሁሉ
እርሱ ያውቃል ወድቀን እንስገድለት
የኛ ንጉስ ተወልዷል በበረት
ከአድማስ ባሻገር ካይናችን የራቀ
ከሩቁ ስናየው ሰማይ የወደቀ
ነገር ግን ያራቱም መጨረሻ አንተ ነህ
ፍጥረት እጅህ ላይ ነው ምን ያህል ትልቅ ነህ
በእውነት እኛም አናውቅህም
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ ካይምሯችን በላይ ጥልቅ ነው ችሎታህ
ስራዎችህ ሁሉ ስላንተ አወሩ
ይሁን ስትላቸው ሆኑ ፍጥረታት በሙሉ
ክብር ለስምህ ይሁን
ነፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል
የበረዶ ክምር ማን አጥቦ አንጽቶታል
ምድርን ስትሰራ ማን ነበረ አብሮህ
እንዲህ አድርግ ብሎ ማንስ አማከረህ
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑህ
እልፍ አእላፍ መልአኮች ወድቀው የሚሰግዱልህ
በእውነት አንተ እግዚአብሔር ነህ/2/
ስራህን ለመግለጽ አንደበት ቢያንሰኝም
ከምስጋና በቀር የምለው የለኝም
ሳወራው ኖራለሁ እስከለዘላለም
ያረከው ሁሉ ከልቤ አይጠፋም
ጊዜው ቢርቅ ብዙ ቢያልፍም
ከልቤ ውስጥ ከቶ አይጠፋም
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ትዝ ይለኛል እስከዘላለም
ዘላለም አይጠፋም የሱስ ፍቅርህ
ያደረከው ሁሉ ውለታህ
ከቶ አልረሳውም ታትሟል በልቤ
የዘላለም ፍቅሬ ነህ ወዳጄ
መገረፍ መድማትህ ለኔ መሞትህ
ከጥፋት እንዳመልጥ ከክብርህ መውረድህ
ከተወጋው ጎንህ የፈሰሰው ደምህ
ዘወትር ትዝ ይለኛል ኢየሱስ ፍቅርህ
የመስቀሉ ውለታ ለኔ
ትልቅ ትዝታ ነው መድህኔ
ህይወትህን ሰጥተህ አድነኸኛል
ፍቅርህ ከልቤ ውስጥ እንዴት ይጠፋል
አይኔ ሌላ ከቶ አያይም
ምርጫዬ ነህ ለዘለአለም
ፍቅርህ ልቤ ውስጥ ሰርፆ ገብል
ማንም ሳይቀይረው ይኖራል
አመልክሀለሁ አንተን/3/
እያየሁ ፊትህን
ልጅህም እንደሆን ስልጣን ሰጠኽኛል
በቤትህ ዘላለም ልኖር መርጠኽኛል
ምን አይነት ፍቅር ነው ስግደት ይገባኽል /2/
ኢየሱስ ጌታዮ አምላኬ..
አለኝታ ጋሻዮ
መድህኔ
ክብሬ ጌጤ ነህ
እድል ፈንታዮ
ደዌያችንን ፈወሰልን ሀሌሉያ
በፀጋና በምህረቱ ሀሌሉያ
ከዘላለም ሞት ተቤዠን ሀሌሉያ
ለክብሩ እንድንቆም ሀሌሉያ
የምስጋናን መስዋዕት ወደቤትህ ደስ እያለን እናቀርባለን
ለስምህም ክብር ሁልጊዜ በደስታ እንዘምራለን
ሀሌሉያ/2/
ኑና እግዚአብሔርን እናመስግን
ሀሌሉያ/3/
ላመስግነው/2/ ለኔ የሞተውን በግ
ክብር ስጡ ሰዎች ሁሉ
በደሙ አንጽቶናልና
አልተረሳሁም/3/ በስሜ ያውቀኛል/2/
ኦ ያውቀኛል